Choose your meal
መኮረኒ በፈረንጅ ቃሪያ Recipe Ingredients ► 1/2 ኪሎ መኮሮኒ
► 150 ግራም የፈረንጅ ቃሪያ
► 200 ግራም ቲማቲም
► 1 ግንድ ናና
► 4 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
► 4 ሾርባ ማንኪያ ዘይት
► ጨውና ቁንዶ በርበሬ
Process ■ በትልቅ ድስት ውስጥ 2 ሊትር ውሃ ና ጨው አፍልቶ መኮለኒውን መቀቀል ና ማጥለል
■ ቲማቲሙን በደንብ አጥቦ በረጃጀሙ መቆራረጥ
■ የፈረንጀ ቃሪያውን አጥቦ በክብ ፍሬውን አውጥቶ እንደቲማቲሙ መቆራረጥ
■ ነጭ ሽንኩቱን ልጦ፣ አጥቦ በክብ መቆራረጥ
■ ናናውን በጨርቅ ጠርጎ በትንንሹ መክተፍ
■ በመጥበሻ ዘይት አግሎ ነጭ ሽንኩርቱን ማቁላላት
■ የተከተፈውን ቲማቲማና የፈረንጅ ቃሪያ ውድ ነጭ ሽንኩርቱ ጨምሮ መጠባበስ፣
■ የተቀቀለውን መኮረኒ የተደበላለቀውን ቲማቲምና የፈረንጅ ቃሪያ ውስጥ መጨመር
■ ጨው፣ ቁንዶ በርበሬና ናና ጨምሮ አዋህዶ ማቅረብ።

