| ምላስና ሰንበር በሚጥሚጣና በበርበሬ Recipe |
| Ingredients |
► 150ግራም ምላስ በደንብ ታጥቦና ተልጦ የተከተፈ ► 150ግራም ጨጓራ ተፍቆና በደንብ ታጥቦ የተከተፈ ► 200 ግራም ሽንኩርት በቁመቱ የተቆረጠ ► 1 የሻይ ማንኪያ አፍርንጅ ► 150ግራም ለጋ ቅቤ ► 1የሻይ ማንኪያ ሚጥሚጣ ሁለት የሻይ ማንኪያ በርበሬ ► 2 የሾርባ ማንኪያ በደቃቁ የተከተፈ ቃሪያ ► ጨው ► ቁንዶ በርበሬ
|
 |
| Process |
■ ጨጓራውን በቀዝቃዛ ውሃ በደንብ አጥቦ ለመፋቅ እንዲመች የፈላ ውሃ ውስጥ ጨምሮ እያወጡ በደንብ መፋቅና ከትፎ በመጥበሻ ላይ ሞቅ ሞቅ እያደረጉ መጭመቅና ሽንኩርቱን መጥበሻ ላይ በቅቤ ማቁላላትና የተጨመቀውን ጨጓራ ከሽንኩርት ጋር ማቀላቀልና እያማሰሉ ማዋሃድና ምላሱን መጨመርና አፍርንጅና ሚጥሚጣውን ወይም በርበሬውን ነስንሶ ማማሰልና ምላስና ሰንበሩለቁርስ የሚቀርብ በመሆኑ መጥበሻ ላይ በሚበስልበት ጊዜ በጣም እንዳይበስል መጠንቀቅ በጨው ■ በቁንዶ በርበሬ ■ በቃሪያ ቀምሞ በትኩሱ ማቅረብ
|
|
|
| |
| |
| |
| |