EXTERIOR

በግ ጥብስ በቴምር እና በቲማቲም Recipe
Ingredients
► 1/2 ኪሎ የበግ ስጋ
► 2 ፍሬ ቀይ ሽንኩርት
► 6 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
► 2 የቡና ስኒ ቴምር
► 1/2 ኪሎ ቲማቲም
► 6 ብርጭቆ ውሃ
► 1 ሾርባ ማንኪያ በርበቤ
► 1 ፍሬ ሎሚ
► 3 የሾርባ ማንኪያ የስጎ ቅጠል
► 1 ስኒ ዘይት
► ጨው
► ቁንዶ በርበሬ
Process
■ የበጉን ስጋ አጥቦ በመካከለኛ ቅርፅ መቆራረጥ
■ ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርት ልጦ፣ አጥቦ በሽሪሚሪ መክተፍ
■ ቴምሩን ፍሬውን አውጥቶ በሽሪሚሪ መልክ መክተፍ
■ ቲማቲሙን አጥቦ ፣ ልጦ በደቂቁ መክተፍ
■ የስጎ ቅጠሉን አጥቦ በደቃቁ መክተፍ
■ በትልቅ ድስት ዘይት አግሎ የተቆራረጠውን የበግ ስጋ በደንብ መጥበስ
■ የተከታተፉትን ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርት ስጋው ውስጥ ጨምሮ መጥበስ
■ በርበሬ ጨምሮ እንደገና በደንብ መጥበስ
■ የሚጠበሰው ሥጋ ላይ ቲማቲምና ውሃ ጨምሮ ውሃ እስኪመጥ ድረስ ድስቱን ከድኖ ማብሰል
■ የተከተፈውን ቴምር ወደ ስጋው ጨምሮ እንደገና ለትንሽ ደቂቃ ማብሰል
■ ሎሚ ጨምቆና የተከተፈው የስጎ ቅጠል መጨመር ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ ማደበላለቅ
■ አውርዶ ከሩዝ ጋር ማብሰል።